www.goolgule.com/the-unknown-killers-of-beaalu-girma/ /
ethiopia
ዓርብ 27 ሜይ 2016
እሑድ 22 ሜይ 2016
የአገዉ ህዝቦች እና የላስታ - (ዛጉዌ) ስርወ መንግስት ታሪክ
የአገዉ ህዝቦች እና የላስታ - (ዛጉዌ) ስርወ መንግስት ታሪክ
በዶ/ር አያሌዉ ሲሳይ ክፍል አንድ አሰልች እንዳይሆን በአጨር
መንገድ አቀርበዋለሁ መልካም ንባብ:: ስለ ሰዉ ልጅ ዘር
አመጣጥ የተመራመሩ ሊቃዉንት ሁለት ንድፈ ሃሳቦችን
ያስቀምጣሉ:: ከእነዚህ አንደኛዉ የስነ ፍጥረትን አመለካከት
የሚያራምድ ሲሆን : ሁለተኛዉ ግን ሳይንሳዊ አመለካከትን
የሚከተል ነዉ:: የስነ ፍጥረትን አመለካከት በሚያራምደዉ
አባባል መሰረት በቅዱስ መጸሃፍ ዉስጥ ከዘፍጥረት ጀምሮ
እንደሚነበበዉ መሬት ከነልብሱ ሰማይ ከነግሱ የተፈጠሩት
በእግዚአብሔር ነዉ:: ሁለተኛዉ አባባል እንደሚለዉ ከሆነ: ግን
የሰዉ ዘር እምሃበ አልቦ ከትንንሽ ፍጥረታት በመነሳት ቀስ በቀስ
እያዘገመ መጥቶ አሁን ወዳለበት የእድገት ደረጃ ሊደርስ
ችሏል:: ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩም በቅድሚያ "ሆሚኒድስ"
የሚል ስያሜ የነበራቸዉ ሰዉ - መሰል የሆኑ የሰዉ ልጅ ቅድመ
አያቶች : ከ40-25 ሚሊየን በፊት በሚሆኑ አመታት ዉስጥ
በመሬት ላይ የተከሰቱ ሲሆን : በኢትዮጵያም የ3.5 ሚሊየን
አመታት እድሜ በስነ ቁፋሮ ሊቃዉንት የተቸራች ሉሲ ወይም
ድንቅነሽ እና ከ4 ሚሊየን አመት አስቀድሞ እንደነበረ
የሚነገርለት ራሚዳስ አርዲፒተካስ የዚሁ አካል ናቸዉ:: ከዚያ
በመቀጠል ደግሞ "ሆሞ ሀቢለስ" ማለት በእጁ ለመጨበጥ
ችሎታ የነበረዉ ሰዉ የሚመስል እንሰሳ ከ2 ሚሊየን አመታት
በፊት በምድረ ኢትዮጵያ በኦሞ ሸለቆ ብቅ እንዳለ ጥናቶች
ይጠቀሙናል:: በመከተልም ሆሞ ኢሬክተስ ማለት በሁለት
እግሮቹ ቀጥ ብሎ ቆሞ መሔድ የሚችልግንባር ቀሰም ሰዉ -
መሰል እንሰሳ 1 ሚሊየን አመታት ከአሁኑ ዘመን አስቀድሞ
በኮንሶ ጋርዱላ: በአዋሽ ሸለቆ : በመልካ ቁንጡሬ አከባቢ
እንደኖረ በጥናት ተረጋግጧል:: በመጨረሻም (ሆሞ ሳፒየንስ)
ማለት ብልህ ሰዉ - መሰል እንስሳ ከአሁኑ የሰዉ ዘር ጋር
በሁሉም መልኩ የሚቀራረብ : 100,000 አመታት በፊት
በአፍሪካ መኖሩን አጥኝዎች ዘግበዋል:: በኢትዮጵያም በአዋሽና
በኦሞ ሸለቆዎች እንዲሁም : በድሬዳዋ አከባቢ እንደተገኘ
መዛግብት ያስረዳሉ:: ዘመናዊዉ ሰዉ ለመጀመሪያ ግዜ በዚች
መድር ላይ የተከሰተዉ ግን : ከ40000 አመታት በፊት በሆኑን
የስነ ቁፏሮ ሊቃዉንት ይመሰክራሉ:: እንግዲህ ይህን አዝጋሚ
የሰዉን ልጅ የእድገት አመጣጥ ደረጃ ለመመርመር ሳይንሳዊ
የሆነዉን አባባል ከተከተልን : በዚህች ምድር የሚኖረዉ ነጭም
ሆነ ጥቁር ወይም ሌላ ቀለም ያለዉ ህዝብ : የሴም ሆነ የኩሽ
አለበለዚያ የያፌት ዘር: ከዚያም ዉጭ የሆነ የሰዉ ዝርያ :
ከአህጉረ አፍሪካ በተለይም በምድረ - ኢትዮጵያ ተጸንሶ ዝግመተ
- ለዉጡንና እድገቱን ጨርሶ ወደ ሌሎቹ አህጉራት -አለም
ተበታተነ: ለማለት እንገደዳለን:: ከስነ ፍጥረት ንድፈ - ሃሳብ
ተነስተን ቅዱስ መጸሃፍን ምንጭ ካደረግን ደግሞ: አፍሪካ
በመካከለኛዉ ምስራቅ በእግዚአብሔር እጅ ከተፈጠረዉ
ከመጀመሪያዉ ሰዉ ከአዳም ዘር ሲወርድ ሲዋረድ እንደመጣ
የሚነገርለት የኩሽ ዘሮች መኖሪያ ነበረች : አሁንም ናት:
ለመደምደም እንችላለን:: በምድረ ኢትዮጵያ በጥንተ ነዋሪነት
የሚታወቁት የአገዎች ቅድመ - ቅድመ አያቶችም: ከኩሽ
ዝርያዎች አንደኛዉ እና አንጋፋዉ አካል በመሆናቸዉ በስነ -
ፍጥረት አባባል መነሻነት ከመካከለኛዉ ምስራቅ : ገና ጥንታዊ
የጋርዮሽ ስርአተ - ማህበር ዘይቤን ይከተሉ ከነበሩት ኩሻዊያን
ወገኖቻቸዉ ተነጥለዉ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ቀዳማዊያን
ነዋሪዎች ተባሉ? ወይስ እንደ አዝጋሚዉ የሰዉ ዘር አመጣጥ
አስተሳሰብ ከዚሁ ከምድረ ኢትዮጵያ ተጸንሰዉ: ዝግመተ
ለዉጣቸዉን አጠናቀዉ ካሁኑ የዘመናዊ ሰዉ መከሰት ደረጃ ላይ
ደረሱ? የሚሉትን ሁለት አቀራረቦች መመርመር: የታሪክ ግዴታ
ነዉ:: ስለዚህም: የአገዎች ቅድመ - ቅድመ አያቶች የኢትዮጵያ
ጥንተ ነዋሪዎች መሆናቸዉን የሚያረጋግጡ መረጃዎችን ዋቢ
በማድረግ ከየት - መጣ ታሪካቸዉን በዚህ መጸሃፍ የመጀመሪያ
ምእራፍ ላይ ሰፋ በማድረግ ለአንባቢያን ለማቅረብ ሙከራ
አደርጋለሁ:: የአተራረኬም ስልትም የዝግመተ ለዉጥን አቀራረብ
ሳይዘነጋ በአብዛኛዉ ከስነ ፍጥረት አተራረክ ጋር በተዛመደ
መልኩ የሚታወቀዉን : የነገደ - ኩሽ አመጠጣጥ ላይ
የተመረኮዘ ነዉ:: ጥንተ አቅኝዎች የአገዎች ቅድመ - ቅድመ
አያቶች የሆኑት ሰዎች ከሌሎች የኩሽ ነገድ ወገኖቻቸዉ ጋር
በመሆን በአሜን እና ማእከላዊ የጥንት ኢትዮጵያ መሬቶች
በሚኖሩበት ግዜ አንድ ወጥ በሆነ የአጠራር ስያሜ ይታወቁ
የነበረ ሲሆን : ከደቡብ አረባዊያን (ሳባዊያን መምጣት ቡሃላ
ግን የተወሰኑት የአገዎች ቅድመ - ቅድመ አያቶች ነባሩን
ባህላቸዉን ከመጤዎቹ ባህል ጋር ሲያዋህዱ ቀሪዎቹ
ማንነታቸዉን እንደጠበቁ በሰሜንም ይሁን (የቢለንን አገዎች
እንደምሳሌ መዉሰድ ይቻላል) በደቡብ መኖሪያቸዉን
አመቻችተዉ ቆይተዋል:: ግዜ አልፎ ጊዜ ሲተካ ደግሞ : ደረጃ
በደረጃ እስከ ስምንት ቁጥር የሚደርሱ የአገዉ ህዝቦች
ቅርንጫፎች የተፈጠሩ መሆናቸዉን በዚሁ በመጀመሪያዉ ምእራፍ
ገለጽ አድርጌዋለሁ:: በተለይ በጥንት ኢትዮጵያ ስልጣኔ
ሳይታቀፉ እራሳቸዉን ችለዉ የኖሩት የአገዉ ነገዶች ከጥንታዊዉ
የአክሱም መንግስት ጦር ሰራዊት ጋር ታላላቅ ፍልሚያዎችን
ያካሔዱ ቢሆንም ከጥቂቶቹ በስተቀር ከሰወስተኛዉ እስከ
አራረኛዉ ድረስ በነበሩበት ምእተ አመታት እየተሸነፉ በዚያዉ
ግዛት ቁጥጥር ዉስጥ ቀስ በቀስ ለመጠቃለል በቅተዋል::
ጥንታዊዉ የአክሱም መንግስትም የአገዉ ህዝቦች ከድሮ ጀምሮ
የነበራቸዉን ወታደራዊ ወኔ እና ጀግንነት በመገነዘብ
በስድስተኛዉ ክፍለ - ዘመን ቁልፍ የጸትታ ማስጠበቅ ቦታዎችን
ሰጥቷቸዉ እንደነበር አሁንም በዚሁ የመጀመሪያዉ ክፍል
ተብራርቷል:: ከዚህ ዘመን ወዲህም ቢሆን: ከአክሱም መንግስት
አፈንግጠዉ የቀሩ አገዎች ስለነበሩ ማመጻቸዉን በመቀጠል
ለዚያ ስርወ መንግስት መዉደቅ : የበኩላቸዉን አስተዋፆዎ
ከማድረጋቸዉም ባሻገር ዙፋኑንም እስከመቀማት ደርሰዋል::
ይህም በበኩሉ የዮዲትን መነሳት ታሪክ ተገን በማድረግ
ተወስቷል:: አገዎች የአክሱምን ጥንታዊ ስልጣኔ ከመሰረቱት
ከሳባዊያን ጋር አንድ ሁነዉ : በአቻነት የበኩላቸዉን ሚና
እንደተጫወቱ ቢታወቅም : በተለይ በ11ኛዉ ክፍለ ዘመን ላይ
በጦርነት ይሁን በሰላማዊ መንገድ ዙፋኑን በእጃቸዉ በማስገባት
ከአክሱም ወደ ላስታ - ዋግ በማዛወር ከሰዎስት መቶ ለሚልቁ
ዘመናት ገዝተዋል:: ይህ የአገዎች መንግስት እስከ ዛሬ ድረስ
ዛጋ በሚል ሰያሜ በሁሉም ጸሀፊዎች የሚታወቅ ቢሆንም :
በዚህ መጸሃፍ ግን የላስታ - ዋግ ስርወ መንግስት በሚል
መጠሪያ ሰጥቼዋለሁ:: በተጨማሪም ነባሩን ስያሜ በቅንፍ
ዉስጥ ለማስቀመጥ ሞክሪያለሁ:: ለዚህም ምክኒያት የሆኑኝ
የአክሱም: የጎንደር: የሸዋ: ወዘተርፈ......መንግስታት በሚሉ
አቀራረቦች የተጻፉ ታሪኮች ናቸዉ:: የዛጉዌ መንግስት ከማለት
በነገስታቱ የትዉልድ ክልል እና በስረወ - መንግስት መናገሻ
ቦታዎች መጠሪያ የላስታ - ዋግ መንግስት ቢባል መሰረት-
መነሻዉን ሊያንጸባርቅ ይችላል የሚልም እምነት አድሮብኛል::
የላስታ- ዋግ ስርወ መንግስት ዘሮች እንደሆኑ በአበዉ አባባል
የሚነገርላቸዉ የዋግ ሹሞች ታሪክም የአገዉ ህዝቦችን የረጅም
ዘመናት የታሪክ ሂደቶች ተከትሎ የመጣና የቀጠለ እንደሆነ
ስለሚታወቅ ከአፈ ታሪክ እና ከተጨባጭ ምንጮች ያገኘሃቸዉን
መረጃዎች መከታ በማድረግ የመጨረሻዉን የመጸሃፍ ክፍል
እንዲይዙ አድርጊያለሁ:: የአገዉ ህዝቦች ታሪክ ከዘመናዊ
የአተራረክ ስርአት የሚነሱት የታሪክ መጽሃፍት በሙሉ: የአገዉ
ህዝቦች በቅዱስ መጽሃፍ አተራረክ መሰረት : ከአዳም ጀምሮ
ሲቆጠር 10ኛ ትዉልድ ላይ የሚገኘዉ የኖህ የልጅ ልጅ ማለት:
የካም ልጅ የሆነዉ ነገድ ዝርያዎች መሆናቸዉን በአጽንኦት
ይተርካሉ:: (ኦሪት ዘፍጥ.10: 6-8) ይህን መነሻ በማረግም
ክቡር አቶ ተክለ ጻድቅ መኩሪያ ከአጼ ልብነ ድንግል እስከ አጸጼ
ቴወድሮስ በሚለዉ የታሪክ መጸሃፋቸዉ በገጽ 2 ላይ : የአገዎች
የዘር ግንድ የሆኑት የኩሽ ዘሮች ከመሰጴጦሚያ ተነስተዉ በአረብ
በኩል በማድረግ ቀይ ባህርን ተሻግረዉ ወደ ኢትዮጵያ ሰሜንና
ወደ አዶሊስ ደሴት መግባታቸዉን : ከዚያም የወገን ስማቸዉንና
ቋንቋቸዉን ብሎም አምልኳቸዉን ለይተዉ እንደኖሩ ቁልጭ
አድርገዉ ተርከዋል:: ከአፈ - ታሪክ የሚጀምሩ ሙህራን ግን:
የአገዉ ህዝቦች: ከሌላኛዉ የኖህ ልጅ ማለት ከሴም ነገድ
ሲወርድና ሲዋረድ የመጡ እና በልዮ ልዮ ዘመናት - ከምድረ
እስራኤል እየፈለሱ በቀጥታ ወደ ዛሬዋ ኢትዮጵያ መሬት የገቡ
መሆናቸዉን ይናገራሉ:: ከነዚህ ሁለት በሃሳብ የሚጋጩ
አባባሎች በመነሳት የአገዉ ህዝቦችንና የነሱ ዝርያ የሆኑትን
የላስታ - ዋግ (ዛጉዌ) ነገስታት መሰረተ አመጣጥ ከስረ -
መሰረቱ ጀምሮ ለመረዳት እንዲያመች : ታሪካቸዉ እራሱን ችሎ
በሚቀጥሉት ገጾች በስፋት እንዲብራራ አድርጌዋለሁ:: የዉጭ
አገር እና እትዮጵያዊያን ጸሃፊዎች ስለ አገራችን ታሪክ በጻፏቸዉ
በርካታ በጸሃፍት ዉስጥ የአገዎችን ታሪክ በመጠኑ ጠቀስ: ጠቀስ
እያደረጉ ማለፋቸዉ አልቀረም : ሆኖም ግን የእነዚህን
ጥንታዊያን እና ነባር የአገዉ ህዝቦች ሙሉ ታሪክ እራሱን
አስችሎ በአንድ መጸሃፍ ሰፋ በማድረግ የጻፈ ሙህር ከቶ
አስከዛሬ አልተገኘም:: የአገዉ ህዝቦች የምድረ - ኢትዮጵያ
ጥንተ ነዋሪዎችና አገሪቱን በግንባር ቀደምትነት ካቀኑት ነገዶች
ዋኖቹ መሆናቸዉን ብዙ የታሪክ ምርምሮችን ያከናወኑ ሊቃዉንት
በመረጃዎችየታገዙ ትንታኔዎችን ቢያቀርቡም : በኢትዮጵያ ህዝብ
ዘንድ በአብዛኛዉ: ብሎም በራሳቸዉ በአገዎች ጭምር እስከ ዛሬ
ድረስ የሚንጸባረቀዉ የዘልማድ አባባሉ ብቻ ነዉ:: ይህን ሁኔታ
ተገን በማድረግ የዘልማድ አባባሎችም ሆኑ: በዘመናዊ መረጃ
የተደገፍ የአተራረክ ዜይቤዎች: ለአንባቢያን በተገቢዉ መንገድ
ቁልጭ ቢለዉ ቢቀርቡ እዉነታዉን የበለጠ ለመረዳት የሚቻል
መሆኑን ግንዛቤ ዉስጥ ለማስገባት ዘንድ እንሆ ሁለቱንም
አተራረኮች በቅደም ተከተል ለማቅረብ ጥረት አደርጋለሁ::
የአገዉ ህዝቦች ታሪክ በአበዉ የዘልማድ አባባል በአገራችን
በኢትዮጵያ በርካታ አፈ ታሪክ አዋቂዎች ከየአባቶቻቸዉ ያገኙትን
ለቀጣዮ ትዉልድ ቃል በቃል የሚያስተላልፍት የዘልማድ አባባል
የአገዉ ህዝቦችን የዘር ሃረግ : ከኖህ ግንድ ከወረደዉ ከሴም
ነገድ ዉስጥ በተለይም ከንጉስ ዳዊት የትዉልድ ዛፍ ጋር:
ያቀናጀዋል:: ይህ አይነቱ አፈ ታሪክ መሰረት ያገኘዉ በቅዱስ
መጽሐፍ ተደጋግማ የተጠቀሰችዉ የንግስት ሳባ (አዜብ) ወይም
ማክዳ የሰለሞንን ጥበብ ለመስማትና ለማየት ወደ ሐገረ
እስራኤል መጓዟን በመንተራስ ነዉ:: (1.ነገስት 10: 1-10:
መጽ. ዜና መዋ. 9: የማቴ. ወንጌ.12:42) አፈ ታሪኩ ንግስት
ሳባን ኢትዮጵያዊት የነበረች እና ከዚችዉ አገር ተነስታ ወደ
እስራኤል የሄደች ያደርጋታል:: ይሁን እንጅ የታሪክ ሊቃዉንት ስለ
እሷ የኢትዮጵያ ንግስት መሆን ከአፈ ታሪክ ሌላ የጹሁፍም ሆነ
ቁሳዊ ተጨባጭ መረጃዎችን ባለማግኜታቸዉ አባባሉን አሉታዊ
አድርገዉ ይዘዉታል:: የንግስት ሳባ ኢትዮጵያዊነት የሚተርከዉ
የዘልማድ የታሪክ መድብል ክብረ - ነገስት በመባል የታወቀ
ሲሆን ለመጀመሪያ ግዜ ከግብጽ ወደ ሃገራችን የገባዉ በዘመነ
አጼ ላሊበላ ነበር:: መጽሃፉ ከኮፕት (ቅብጢ) ቋንቋ ወደ
አረብኛ ከተተረጎመ ቡሃላ ከእስክንድሪያ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ
ወደ ግብጽ ሳይመለስ እስከ 14ኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ
ቆይቷል:: በዘመነ ላሊበላ ክብረ ነገስቱ ያልተተረጎመበት ዋነኛ
ምክኒያትም " ሳይገባቸዉ እና የእስራኤል ነገዶች ሳይሆኑ ህግን
ጥሰዉ በሃይል የነገሱ የዛጉዌ ወገኖች " የሚል ሐረግ የነበረበት
በመሆኑ ነዉ:: ነገር ግን በአጼ አምደ ጺዎን ዘመነ መንግስት
ከ1314-1321 በነበሩበት ይስሐቅ የተባሉ የአክሱም ጽዮን
ንብረ እድ በነበሩና በጓደኞቻቸዉ ሊቃዉንት ከአረብኛ ወደ ግእዝ
ተተርጉሟል:: (ተክለ ጻድቅ መኩሪያ የኢትዮጵያ ታሪክ: አክሱም:
ኑቢያ: ዛጓ ገጽ 433) ታሪከ ነገስቱ የኢትዮጵያ ነገስታት ሳባ
ከሰለሞን በወለደችዉ በቀዳማዊ ሚኒሊክ አማክኝነት የዳዊት
ዝርያነት እንዳላቸዉ የሚነገር የዘልማድ አባባል ሲሆን
በእስክንድሪያ መንበረ ፓትሪያርክ ዉስጥ የሰለሞን ዘሮች ነን
ይሉ የነበሩትን ወክሎ በኮፕት(ቅብጢ) ቋንቋ መጀመሪያ የጻፈዉ
ማን እንደሆነ የሚያስረዳ ሰነድ ሊገኝ አልቻለም:: ምናልባት
ከዉጭ ከባእድ አገር ቋንቋ እንደተጻፈ ቢነገር ለጉዳዩ ክብደት
ይሰጠዋል:: እስክንድሪያም ለእየሩሳሌም ቅርብ ስለሆነች ታሪኩ
ከዚያዉ በዉጭ ልሳን ከተጻፈ እዉነት ሆኖ ተቀባይነትን ያገኛል
በማለት ዙፋናቸዉን በላስታ ዋግ የአገዉ ነገስታት የተቀሙት
የጥንቱ የአክሱም መንግስት ተሸናፊ መሳፍንት በምድረ ግብጽ
ዉስጥ ይኖሩ በነበሩ የቅብጢ ልሳን ተናጋሪዎች መነኮሳት
አጽፈዉ ህጋዊያን የዘዉድ ወራሽነታቸዉን ሊያስመሰክሩ
የሞከሩበት አፈ ታሪክ ይሆናል የሚል ግምታዊነት የተላበሰ
አነጋገር መሰንዘር ይቻላል:: በቅዱስ መጸሐፍ ዉስጥ ግን
በማንኛዉም ጥቅስ ቢሆን ንግስት ሳባ ከደቡብ ተነስታ ወደ
ሰለሞን መሔዷ እንጅ ከእሱ ልጅ መዉለዷ ፈጽሞ አልተወሳም::
ከታሪክ አኳያ አባባሉ ሲመረመር ደግሞ መጽሐፍ እንደ
ተፈለሰፈባት ከሚነገርባት ከእስክንድሪያም ሆነ የነገስታቱ የዘር
ሐረግ ተመዘዘ ከተባለበት ከእየሩሳለም በተመሳሳይ አቀራረብ
የሚወሳ መረጃ ባለመገኘቱ ከተረትነት ያለፈ ሊሆን ከቶ
አይችልም:: ይህ ታሪክ ንግስተ ሳባ የኢትዮጵያ ንግስት የነበረች
መሆኗን በማረጋገጥ የሰለሞንን ጥበብ ለመቅሰም ከአክሱም
ተነስታ ወደ እየሩሳለም በተጓዘችበት ወቅት ከንጉሱ ከሰለሞን
ሚኒሊክ የተባለ ወንድ ልጅ እንደወለደች እና እሱም የዳዊት
ዘርነቱን ይዞ በመላዋ ኢትዮጵያ እንደነገሰ ከዚያም የሱ ዘሮች
እስከ መጨረሻዉ የአክሱም ንጉስ እስከ ድልነአድ ድረስ
መንገሳቸዉን በዝርዝር ያስቀምጣሉ::
ረቡዕ 4 ሜይ 2016
ያልነገርኩሽ ነገር
ዓርብ 22 ኤፕሪል 2016
አልወድሽም እንጂ
አልወድሽም እንጂ
______[][][]___________
አልወድሽም እንጂ እኔ ከወደድኩሽ
ያዩሽም አይኖሩ ይቅርና የነኩሽ::
አልወድሽም እንጂ ከወደድኩሽማ
አደባባይ ቆሜ ከመሃል ከተማ
በጂጉ በሚልቅ ከወፎቹ ዜማ
አዜምልሽ ነበር ህዝብ ሁሉ እንዲሰማ::
ያው እንደነገርኩሽ
አልወድሽም እንጂ እኔ ከወደድኩሽ
ፅሀይ ትቆማለች ጨርቃም አትወጣም
ነፋሱም ፅጥ ይላል ብርዱም አይበረታም::
ወንዞችም አይፈሱም ቆመው ይሰማሉ
የፍቅራቸው ነገር ዕፁብ ነው እያሉ::
ከፍቅራችን በላይ እጅግ የሚገርመው
እኛ ስንጎዳ ህዝቡን ነው የሚያመው::
አልወድሽም እንጂ !
አልወድሽም እንጂ !
እኔ ከወደድኩሽ
ያው እንደነገርኩሽ
አመት አንድ ቀን ነው በፊትሽ በፊቴ
ምድርም አንድ እርምጃ ላንቺ ና ኔ ኮቴ::
እኔማ ስወድሽ
ሰማይ ትጠባለች በፍቅራችን ደስታ
እኛ ከፈለግን ቀን ይሆናል ማታ::
እምልልሻለሁ "አልወድሽም እንጂ ከወደድኩሽ ብዬ"
ደስ አሰኝሻለሁ ሰጎንን ቀድሜ አንበሳን ታግዬ::
እኔ ከወደድኩሽ
እየተራመድን ነፋስ እንቀድማለን
እየተናገርን ዓለት እንሰብራለን
ከደመና መሃል ደመና እንፈጥራለን ::
አትጠራጠሪ
አልወድሽም እንጂ የወደድኩሽ ዕለት
ብረት እና ሳት ነን አንቺ ና ኔ ማለት::
እሳት ና ብረት ግጥም እና ዜማ
ንጉስ እና ንግስት እግር እና ጫማ
አንድ መሆን ታውቂያለሽ አንድ መልክ አንድ ቀለም
እኔ አንችን ስወድሽ የሚመስለን የለም::
ግን
እኔ ከማልኩልሽ በሚበልጥ መሃላ
ከምድራዊው ፍቅር ባይደለ በሌላ
አለት በሆነ ልብ በማይጎድል ተስፋ
በማይናድ ፅናት ቅፅበት በማይጠፋ
በውበትሽ ሰክረው ቅኔ እየዘረፉ
በነበልባል ፍቅርሽ ነደው እየጠፉ
የሚወዱሽ አሉ
እኔ ከወደድኩሽ ታዲያ እነዚህ ሰዎች ምንድን
ይሆናሉ........ምንጭ fb.
ⓑⓘⓡⓤⓚ ⓩ ⓐⓖⓔⓦ