ዓርብ 22 ኤፕሪል 2016

አልወድሽም እንጂ

አልወድሽም እንጂ
______[][][]___________
አልወድሽም እንጂ እኔ ከወደድኩሽ
ያዩሽም አይኖሩ ይቅርና የነኩሽ::
አልወድሽም እንጂ ከወደድኩሽማ
አደባባይ ቆሜ ከመሃል ከተማ
በጂጉ በሚልቅ ከወፎቹ ዜማ
አዜምልሽ ነበር ህዝብ ሁሉ እንዲሰማ::
ያው እንደነገርኩሽ
አልወድሽም እንጂ እኔ ከወደድኩሽ
ፅሀይ ትቆማለች ጨርቃም አትወጣም
ነፋሱም ፅጥ ይላል ብርዱም አይበረታም::
ወንዞችም አይፈሱም ቆመው ይሰማሉ
የፍቅራቸው ነገር ዕፁብ ነው እያሉ::
ከፍቅራችን በላይ እጅግ የሚገርመው
እኛ ስንጎዳ ህዝቡን ነው የሚያመው::
አልወድሽም እንጂ !
አልወድሽም እንጂ !
እኔ ከወደድኩሽ
ያው እንደነገርኩሽ
አመት አንድ ቀን ነው በፊትሽ በፊቴ
ምድርም አንድ እርምጃ ላንቺ ና ኔ ኮቴ::
እኔማ ስወድሽ
ሰማይ ትጠባለች በፍቅራችን ደስታ
እኛ ከፈለግን ቀን ይሆናል ማታ::
እምልልሻለሁ "አልወድሽም እንጂ ከወደድኩሽ ብዬ"
ደስ አሰኝሻለሁ ሰጎንን ቀድሜ አንበሳን ታግዬ::
እኔ ከወደድኩሽ
እየተራመድን ነፋስ እንቀድማለን
እየተናገርን ዓለት እንሰብራለን
ከደመና መሃል ደመና እንፈጥራለን ::
አትጠራጠሪ
አልወድሽም እንጂ የወደድኩሽ ዕለት
ብረት እና ሳት ነን አንቺ ና ኔ ማለት::
እሳት ና ብረት ግጥም እና ዜማ
ንጉስ እና ንግስት እግር እና ጫማ
አንድ መሆን ታውቂያለሽ አንድ መልክ አንድ ቀለም
እኔ አንችን ስወድሽ የሚመስለን የለም::
ግን
እኔ ከማልኩልሽ በሚበልጥ መሃላ
ከምድራዊው ፍቅር ባይደለ በሌላ
አለት በሆነ ልብ በማይጎድል ተስፋ
በማይናድ ፅናት ቅፅበት በማይጠፋ
በውበትሽ ሰክረው ቅኔ እየዘረፉ
በነበልባል ፍቅርሽ ነደው እየጠፉ
የሚወዱሽ አሉ
እኔ ከወደድኩሽ ታዲያ እነዚህ ሰዎች ምንድን
ይሆናሉ........ምንጭ fb.
ⓑⓘⓡⓤⓚ ⓩ ⓐⓖⓔⓦ

ሐሙስ 21 ኤፕሪል 2016

ብሩክ

►በሕይወት ውስጥ አንዴ ከሄዱ የማይመለሱ ሦስት ነገሮች
☞ ጊዜ፣ ቃል እና አጋጣሚ
►በሕይወት ውስጥ ልታጣቸው የማይገቡ ሦስት ነገሮች
☞ ሰላም፣ ተስፋ እና ታማኝነት
►በሕይወት ውስጥ እጅግ ዋጋ ያላቸው ሦስት ነገሮች
☞ ፍቅር፣ እምነት እና ባልንጀሮች
►በሕይወት ውስጥ እርግጥ ያልሆኑ ሦስት ነገሮች
☞ ሕልም፣ ስኬት እና እድል
►አንድን ሰው ሰው የሚያደርጉ ሦስት ነገሮች
☞ጠንክሮ መስራት፣ ቅንነት እና ጽናት
►በሕይወት ውስጥ አንድን ሰው ሊያጠፉ የሚችሉ ሦስት
ነገሮች
☞ ሱስ፣ ትዕቢት እና ጭንቀት
ከመፅሐፍት አለም